ክሬቲቭ
ኪንግደም

የፈጠራ ኢንዱስትሪ ለመገንባት 100,000 ሰዎች ብቻ እንደሚወስድ ያውቃሉ?

ክሬቲቭ ኪንግደም ፕሮጀክቶች

ሰዋስው መልቲሚድያ

ሰዋስው ፖድካስቶች ኔትዎርክ

ክሬቲቭ ኪንግደም ምንድን ነው?

ክሬቲቭ ኪንግደም የበጎ ፈቃድ ድርጅት ኢትዮጵያን ከሰው ዘር መገኛ ወደ ፈጣሪ ትውልድ ለማምጣትና፤ ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የፈጠራ እና የምርምር ችሎታ ወይም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍ፣ ፖሊሲ ለውጥ ለማስገኘትና ለሀገር ፍሬያማ ትውልድ ለማፍራት የተደራጀ ሀገር በቀል ተቋም ነው።

የምንሰራቸው ስራዎች

  • ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር ፖሊሲ ለውጥ ማስገኘት
  • የፈጠራ እና የምርምር ችሎታ ወይም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች መደገፍ ለሀገር ፍሬያማ ትውልድ ማፍራት
  • የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን ወጣቶች ከአጋሮቻችን ጋር በማገናኘት ስፖንሰር ማስተካከል
group, children, boy-3137670.jpg

አዲስ የፈጠራ ሐሳብ አለዎት?
ወይንስ ኢንደስትሪ የማሻሻል ዕቅድ አለዎ?

እንግዲያውስ የክሬቲቭ ኪንግደም አባል በመሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ይሁኑ

ክሬቲቭ ኪንግደም የበጎ አድራጎት የሚያስተባብራቸው

ወጣት ፈጣሪዎች

ወጣቱ ትውልድ የሃገር ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን አዲስ እና ነባር የእውቀት መንገዶችን በመተግበር እና እንቅፋቶችን በመቋቋም ልዩ ልዩ ፈጠራዎችን መስራት አለበት። ። ህብረተሰቡ ወጣት ፈጣሪዎችን የታሪክ፣ የግብአት እና የዕድሎች መናኸሪያ በመስጥት ሲያበረታታ፣ ወጣቱ ደግሞ እነዚህን የፈጠራ ሃሳቦችን ወደ መሬት ለማውረድ የገንዘብ፣ ጊዜ እና የእውቀት ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ የፈጣሪ ትውልድ መገንባት እንችላለን።

ማሕበረሰብ

እንደ ማህበረሰብ ሰዎች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ በመፍቀድ፣ በህብረተሰባችን ውስጥ የፈጠራ ሀሳባቸውን ማጠናከር ፣የሚመጡትን አዳዲስ ፈጠራዎች ለመረዳት መሞከር፣ ፖሊሲዎችን በመቀበል ፣ ፈጠራን ማበረታታት እንዳለብን ሁሉ በፈጠራ ኢንደስትሪው ላይ የህብረተሰቡ ሚና የሚያመጣውን ተጽእኖ በመገንዘብ ይህን ትውልድ መደገፍ፣ ማበረታታት፣ ባህላዊ አስተሳሰቦችን ማስወገድ ወደምንገነባው ግዙፍ የፈጠራ እና የለውጥ ጉዞ ይመራናል።

መንግስት

እንደ መንግስት ከፈጠራ ኢንዱስትሪዎቻችን ራዕይ ጀርባ በመቆም፣ ህብረተሰቡን በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በመምራት፣ የህዝቡን የፈጠራ ተነሳሽነት እና ፍሰት ለማበረታታት ህጎች መቀረፅ አለብን።የፈጠራ ኢንዱስትሪዎቻችንን ወደ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለመቀየር መንግስት የፈጠራ ትውልዱን በመደገፍ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን በማውጣት ልንገነባ ያሰብነውን ትልቅ ፈጣሪ ትውልድ መፍጠር እንችላለን።

እምቅ የፈጠራ ችሎታ እናበረታታ!​

የክሬቲቭ ኪንግደም አባል በመሆን የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆኑትን ወጣቶችን እንርዳ​

ወጣቱ ትውልድ ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በላይ ለውጥ ማምጣት ይችላል

ወጣቱ ትውልድ ለአዳዲስ የፈጠራ ስራዎች ሁሌም አይምሮውን ክፍት የሚያደርግ ፣ያለፉትን ስኬቶቻችንን እያየ ተስፋ እና ብርታት የሚሆነው፣ ጠንካራ የስራ ፍቅር እና ጥሩ የስራ ስነምግባርን በመላበስ የሚያጋጥሙትን እንቅፋቶች በሙሉ በአይበገሬነት የሚቋቋም ህልሙን ለማሳካት ማንኛውንም አይነት መስዋትነት የሚከፍል ጠንካራ ትውልድ።

ኑ አብረን እንስራ

ወጣቱ ትውልድ የሚፈጥራቸውን አዲስ ሃሳቦች እና ፈጠራዎች
መንግስት በማሳደግ መደገፍና ፖሊሲ በመቅረፅ ማገዝ አለበት

የፈጠራ ኢንዱስትሪን ለመገንባት 100,000 ሰዎች ብቻ እንደሚያስፈልጉ ያውቃሉ?

የክሬቲቭ ኢኮኖሚውን ይቀላቀሉ!

ኢንዱስትሪን የሚያሻሽል ፅንሰ-ሀሳብ አለዎት?

ወደ ክሬቲቭ ኪንግደም በመመዝገብ ጽንሰ ሃሳብዎን እውን እናድርግ
አባል በመሆን፣ የፖሊሲ፣ የገንዘብ እና የማህበራዊ ድጋፍ በማግኘት የፈጠራ ሀሳቦችዎን እና የኢንዱስትሪ አሻሻይ እቅዶችዎን በባለሀብቶች እና በአማካሪዎች እገዛ እውን ማድረግ ይችላሉ።

አጋር መሆን ይፈልጋሉ?

ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ በመሙላት ለወጣት ፈጠራ-ጅማሮች ያለዎን ድጋፍዎን ያሳዩ

በCreative kingdom እንደ አጋር በመሆን፣ የትኞቹን ፕሮጀክቶች መደገፍ እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ይችላሉ።