ስለኛ

group, children, boy-3137670.jpg

ለማቋቋም መነሻ የሆኑ ምክንያቶች

  • በአሁን ሰዓት በሀገራችን ካለው አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ የተማሩ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ የመጣ መሆኑ፤
  • የተማሩ ወጣቶች የፈጠራ እና የምርምር ችሎታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ
  • የፈጠራ እና የምርምር ችሎታ ወይም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች መደገፍ ለሀገር ፍሬያማ ትውልድ ማፍራት
    እንዲሁም ቱ ኤፍ ካፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞ ለተነሳው አላማ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን
    ማመናችን፤

ክሬቲቭ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ማህበር ዓላማ

አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን የሚያመነጩ ወጣቶችን ለመደገፍና የፈጠራ ስራቸውን ለማስተዋወቅ፤
በሀገራችን ውስጥ የፈጠራ ስራዎች ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ መገንባት (building creative economy)፤

ሳይንሳዊ፣ ማህበራዊ እና ኪነጥበባዊ የፈጠራ ስራዎችና ግኝቶች እንዲስፋፉ ማበረታት፤

የፈጠራ እና የምርምር ችሎታ ወይም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍ ፍሬያማ

ትውልድ ለሀገራችን ማፍራት፤

በሀገራችን ውስጥ በሚካሄዱት የፈጠራ፣ የምርምር ወይም ልዩ ተሰጥኦ ስራዎችን
የሚመለከቱ ፖሊሲዎች ላይ ለተሻለ እድገት ተጽእኖ መፍጠር 

ክሬቲቭ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ማህበር መስራቾች​

አቶ በኃይሉ ተስፋሁን
ቦርድ መሪ

ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ
ሃይብሪድ ዲዛይንስ, CEO

አቶ አብርሃም ፍቅሩ
2ኤፍ ካፒታል, CEO

ወ/ሮ መሰረት ፍቅሩ
2ኤፍ ካፒታል, ማናጀር

አቶ ሀብቱ ነጋሽ
ሰዋስው መልቲሚድያ, CEO

ክሬቲቭ ኪንግደም የበጎ አድራጎት የሚያስተባብራቸው

ወጣት ፈጣሪዎች

ወጣቱ ትውልድ የሃገር ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን አዲስ እና ነባር የእውቀት መንገዶችን በመተግበር እና እንቅፋቶችን በመቋቋም ልዩ ልዩ ፈጠራዎችን መስራት አለበት። ። ህብረተሰቡ ወጣት ፈጣሪዎችን የታሪክ፣ የግብአት እና የዕድሎች መናኸሪያ በመስጥት ሲያበረታታ፣ ወጣቱ ደግሞ እነዚህን የፈጠራ ሃሳቦችን ወደ መሬት ለማውረድ የገንዘብ፣ ጊዜ እና የእውቀት ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ የፈጣሪ ትውልድ መገንባት እንችላለን።

ማሕበረሰብ

እንደ ማህበረሰብ ሰዎች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ በመፍቀድ፣ በህብረተሰባችን ውስጥ የፈጠራ ሀሳባቸውን ማጠናከር ፣የሚመጡትን አዳዲስ ፈጠራዎች ለመረዳት መሞከር፣ ፖሊሲዎችን በመቀበል ፣ ፈጠራን ማበረታታት እንዳለብን ሁሉ በፈጠራ ኢንደስትሪው ላይ የህብረተሰቡ ሚና የሚያመጣውን ተጽእኖ በመገንዘብ ይህን ትውልድ መደገፍ፣ ማበረታታት፣ ባህላዊ አስተሳሰቦችን ማስወገድ ወደምንገነባው ግዙፍ የፈጠራ እና የለውጥ ጉዞ ይመራናል።

መንግስት

እንደ መንግስት ከፈጠራ ኢንዱስትሪዎቻችን ራዕይ ጀርባ በመቆም፣ ህብረተሰቡን በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በመምራት፣ የህዝቡን የፈጠራ ተነሳሽነት እና ፍሰት ለማበረታታት ህጎች መቀረፅ አለብን።የፈጠራ ኢንዱስትሪዎቻችንን ወደ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለመቀየር መንግስት የፈጠራ ትውልዱን በመደገፍ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን በማውጣት ልንገነባ ያሰብነውን ትልቅ ፈጣሪ ትውልድ መፍጠር እንችላለን።

የኢትዮጵያን የክሬቲቭ ኢኮኖሚ አብረን እንገንባ

ጥያቄ አለዎ?
ስለ ንግድዎ ፣ ስለ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ፣ የፈጠራ እድሎች እና እርስዎን እንዴት ልንረዳዎ እንደምንችል ለመነጋገር ሁል ጊዜ ክፍት ነን።

ኢንዱስትሪን የሚያሻሽል ፅንሰ-ሀሳብ አለዎት?

ወደ ክሬቲቭ ኪንግደም በመመዝገብ ጽንሰ ሃሳብዎን እውን እናድርግ
አባል በመሆን፣ የፖሊሲ፣ የገንዘብ እና የማህበራዊ ድጋፍ በማግኘት የፈጠራ ሀሳቦችዎን እና የኢንዱስትሪ አሻሻይ እቅዶችዎን በባለሀብቶች እና በአማካሪዎች እገዛ እውን ማድረግ ይችላሉ።

የፈጠራ ኢንዱስትሪን ለመገንባት 100,000 ሰዎች ብቻ እንደሚያስፈልጉ ያውቃሉ?

የክሬቲቭ ኢኮኖሚውን ይቀላቀሉ!

አጋር መሆን ይፈልጋሉ?

ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ በመሙላት ለወጣት ፈጠራ-ጅማሮች ያለዎን ድጋፍዎን ያሳዩ

በCreative kingdom እንደ አጋር በመሆን፣ የትኞቹን ፕሮጀክቶች መደገፍ እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ይችላሉ።